በሌላ ዜና የ50 ዓመቱ ኤዲ መርፊ፤ የቤተሰብ ፊልሞችን መስራቱን አቁሞ በስታንድ አፕ ኮሜዲ ሊሰራ መወሰኑን “ዘ ሮሊንግ ስቶን” መጽሔት ዘገበ፡፡ ኤዲ መርፊ በሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት የሚደረገውን 84ኛው የኦስካር ሽልማት ስነስርዓት በመድረክ መሪነት እንዲያስተናብር ተሹሟል፡፡ ከ”ሮሊንግስ ስቶን” መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ፊልም የመስራት ጊዜዬ ያበቃ ይመስለኛል ያለው ኤዲ መርፊ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእለት ተእለት ስራው ቤቱ ተቀምጦ ጊታር ሲጫወት መዋል እንደሆነም ተናግሯል፡፡ ኤዲ መርፊ በስታንድ አፕ ኮሜዲ ሲሰራ የነበረው ከ30 ዓመት በፊት ነበር፡፡በሙሉ ስሙ ኤድዋርድ ሬጋን መርፊ ተብሎ የሚጠራው ይህ ዝነኛ ተዋናይ፤ በፊልም ስራ ከ34 ዓመት በላይ ያገለገለ ሲሆን በፊልም ደራሲነት፣ ዲያሬክተርነትና በድምፃዊነትም ሰርቷል፡፡