በሌላም በኩል በሮማን በፍቃዱ መነሻ ሀሳብ ግሩም ብርሃነፀሃይ ስክሪፕት ፅፎለት ሮማን በፍቃዱ ያዘጋጀችው “ሲቲ ቦይዝ” የአማርኛ የፍቅር ድራማ ፊልም ነገ እና ከነገ ወዲያ በመላው አዲስ አበባ ይመረቃል፡፡ መልከ መልካም የከተማ ወጣቶች የተፈጥሮ ተሰጥኦአቸውን ትተው ያልተገባ ገንዘብ ለማግኘት ሲሟሟቱ በሚያሳየው የመቶ ደቂቃ ፊልም ዳግማዊ ፓሪስ ጆርጅ፣ ሮማን በፍቃዱ፣ ያየህራድ ማሞ፣ ዘሪሁን አስማማው፣ ነፃነት ወርቅነህና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል፡፡
በሌላም በኩል ከ70 በላይ ሕገወጥ ቅጂ አዟሪዎች እና አከፋፋዮች አዲስ አበባ በልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አማካኝነት ሕዝቡን ይቅርታ ጠየቁ፡፡ ቢሮው ሱፐርቪዥንና ድጋፍ ሰጪ ኦፊሰር አቶ ፈለቀ ሽኩር ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት አዟሪዎቹና አከፋፋዮቹ ሕጋዊ ቅጂ ለማሰራጨት ዛሬ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው 0118 አዳራሽ ቃል ይገባሉ፡፡