Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 October 2011 11:45

አንፋታም” ትያትርና “ሲቲ ቦይስ” ፊልም ይመረቃሉ “ሕገወጥ ቅጂ አዟሪዎች” ይቅርታ ጠየቁ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በደመና ፕሮሞሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው “አንፋታም” አዲስ ትያትር በመጪው ማክሰኞ በአዲስ አበባ ትያትርና ባህል አዳራሽ ይመረቃል፡፡ አንተነህ ኪዳኔ የደረሰው ይህ ትያትር በምስጋና አጥናፉ ተዘጋጅቷል፡፡ ወይንሸት በላቸው፣ ሄለን ቸርነት፣ ዝናሽ ጌትነት፣ ራሄል ብርሃኑ፣ ኢሳያስ ጥላሁን፣ ልዕልት ሉሉ፣ አንተነህ ኪዳኔ እና ምስጋና አጥናፉ ይተውኑበታል ትያትሩ ዘወትር ማክሰኞ በተመሳሳይ ስፍራ ለሕዝብ እንደሚቀርብም ማወቅ ተችሏል፡፡ ደራሲው ካሁን ቀደም “ዕድል 20”፣ “አይዳ”፣ “ደም”፣ በተሰኙ ትያትሮቹና ጥቁር በለስ በተሰኘ ፊልሙ ይታወቃል፡፡

በሌላም በኩል በሮማን በፍቃዱ መነሻ ሀሳብ ግሩም ብርሃነፀሃይ ስክሪፕት ፅፎለት ሮማን በፍቃዱ ያዘጋጀችው “ሲቲ ቦይዝ” የአማርኛ የፍቅር ድራማ ፊልም ነገ እና ከነገ ወዲያ በመላው አዲስ አበባ ይመረቃል፡፡ መልከ መልካም የከተማ ወጣቶች የተፈጥሮ ተሰጥኦአቸውን ትተው ያልተገባ ገንዘብ ለማግኘት ሲሟሟቱ በሚያሳየው የመቶ ደቂቃ ፊልም ዳግማዊ ፓሪስ ጆርጅ፣ ሮማን በፍቃዱ፣ ያየህራድ ማሞ፣ ዘሪሁን አስማማው፣ ነፃነት ወርቅነህና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል፡፡ 
በሌላም በኩል ከ70 በላይ ሕገወጥ ቅጂ አዟሪዎች እና አከፋፋዮች አዲስ አበባ በልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አማካኝነት ሕዝቡን ይቅርታ ጠየቁ፡፡ ቢሮው ሱፐርቪዥንና ድጋፍ ሰጪ ኦፊሰር አቶ ፈለቀ ሽኩር ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት አዟሪዎቹና አከፋፋዮቹ ሕጋዊ ቅጂ ለማሰራጨት ዛሬ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው 0118 አዳራሽ ቃል ይገባሉ፡፡

Read 3829 times