Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 October 2011 11:42

በሐኪም ትዕዛዝ የሚያስተናግድ ምግብ ቤት ተከፈተ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ክብደት መጨመርና መቀነስ ለሚፈልጉ እንዲሁም በጤና እክል ሐኪም ያዘዘላቸው ደንበኞች የሚመገቡበት ምግብ ቤት (ዳይት ሀውስ) ቦሌ መድሐኔአለም አካባቢ ተከፈተ፡፡ የምግብ ቤቱ ባለቤት ወ/ሮ መሳይ ባዬ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት ለወደፊት የኤሮቢክስ ማዕከል የሚኖረውን ምግብ ቤት እንዲከፍቱ ያነሳሳቸው በተለይ ሕመምተኞች የሚስማማቸውን ምግብ ለማግኘት ሲቸገሩ በማየታቸው መሆኑን ነግረውናል፡፡

በሌላም በኩል ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከአዲስ አበባ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች ለተመረጡ አንድ መቶ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ማሻሻያ ኮርስ ሊሰጥ ነው፡፡ ከአሜሪካ ኤምባሲ በተገኘ 38 ሺህ ዶላር የተጀመረው ኮርስ ከደጃች ባልቻ፣ ሸመልስ ሃብቴ፣ ጥቁር አንበሳ እና አፍሪካ ሕብረት ሁለተኛ ደረጃ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የሚሰጠው ኮርስ ለሁለት ዓመታት ይቀጥላል፡፡ 
ይህ በእንዲህ እንዳለ አርት ሀበሻይ የኪነጥበበ የመረጃና መዝናኛ ማዕከል ለሁለት ወራት በፊልም እና ትያትር ያሰለጠናቸዉን ሰልጣኞች ነገ ከጧቱ 3 ሰዓት ያስመርቃል፡፡ በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት የሚመረቁት ሠልጣኞች የፊልምና የትያትር ሥራዎቻቸውን ለታዳሚ ያቀርባሉ፡፡

 

Read 3857 times Last modified on Saturday, 22 October 2011 11:46