ከአካል ብቃት ግንባታ ስፖርተኝነት፣ ወደ ፊልም ተዋናይነት ከዚያም ወደ ፖለቲካው ገብቶ የካሊፎርኒያ አገረ ገዢ የነበረው ሸዋዚንገር ወደፊልም ስራው ተመልሶ ትወናውን ቀጠለ፡፡ አርኖልድ ሸዋዚንገር በኒው ሜክሲኮ እየተሠራ ባለው “ዘ ላስት ስታንድ” ፊልም ላይ በመሪ ተዋናይነት ይሳተፋል፡፡ በላዩንስ ጊት የሚሠራው ፊልሙ ባለፈው ሰሞን ቀረፃውን በመጀመሩ መደሰቱን የገለፀው አርኖልድ ሸዋዚንገር፤ በአዲሱ ፊልሙ ላይ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ የነበረ አንድ ግለሰብ በአነስተኛ የድንበር ከተማ በሸሪፍነት አገልግሎት የሚሸጥ ገፀባህርይን ይተውናል፡፡