Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 October 2011 11:38

ቴይለር ስዊፍት የቢልቦርድ ምርጥ ሴት ሆነች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ድምፃዊና የዘፈን ደራሲዋ ቴይለር ስዊፍት፤ የቢልቦርድ የዓመቱ ምርጥ ሴት ተብላ መመረጧን ሮይተርስ ከሎስ አንጀለስ ዘገበ፡፡ በ21 ዓመቷ ይህን ሽልማት በማግኘቷም የመጀመሪያዋ ወጣት አርቲስት ሆናለች፡፡ ቴይለር ስዊፍት ሰሞኑን ከሆሊውድ ሪፖርተር ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ፤ ለቀጣይ አልበሟ 25 የዘፈን ግጥሞችን ጽፋ መጨረሷን ተናግራለች፡፡

አራት የግራሚ ሽልማቶችን የወሰደችው ቴይለር ስዊፍት፤ “ስፒክ ናው” የተባለው አልበሟ ለ5 ጊዜያት በሽያጭ የፕላኒቲኒዬም ደረጃ ያገኘ ከመሆኑም በላይ ዘንድሮ በአሜሪካ ከፍተኛ ሽያጭ ካገኙ አልበሞች ግንባር ቀደም ሆኖላታል፡፡ ከዚሁ ዓልበም ላይ 14 ዘፈኖችዋ በቢልቦርድ 100 ትኩስ ዘፈኖች ደረጃ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የቢልቦርድ ዘገባ እንደገለፀው፤ ቴይለር ስዊፊት በዓለም ዙሪያ 20 ሚሊዮን የአልበም ቅጂዎች የሸጠች ሲሆን 40 ሚሊዮን ዘፈኖቿ ከኢንተርኔት መጫናቸውንም አመልክቷል፡፡

 

Read 2837 times Last modified on Saturday, 22 October 2011 11:39