Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 22 October 2011 11:36

ኤሚነምና ሊል ዋይኔ “የሮክ ፈጣሪዎች” ተባሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ራፐሮቹ ኤሚነምና ሊል ዋይኔ ከሮሊንግስቶን ባንድ ጊታር ተጨዋች ኬዝ ሪቻርድስ ጋር “ጐድ ኦፍ ሮክ” በሚል ስያሜ መወደሳቸው ታወቀ፡፡ 43 አርቲስቶችን “ጐድ ኦፍ ሮክ” በሚል ርእስ አወድሶ ዘገባውን የሰራው ጂኪው የተባለ መፅሄት ሲሆን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለንባብ ይበቃል፡፡
ኤሚነም ወደ ራፕና ሂፕሆፕ ሙዚቃ ከመግባቱ በፊት በሮክ ሙዚቃ ስልቶች ሲያቀነቅን እንደነበር የተዘገበ ሲሆን፤ ራፐሩ ሰሞኑን 39ኛ ዓመት የልደት በዓሉን እንዳከበረ ታውቋል፡፡ ኤሚነም ከጂኪው መፅሄት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ በ2000 እኤአ ላይ ዘ ማርሻል ማዘርስ ኤልፒ ብሎ በሰራው አልበሙ 6 ሙዚቃዎችን በሮክ ስልት ሰርቶ እንደነበር አስታውሶ በወቅቱ እነዚህ ዘፈኖች ስለተሰረቁበት በብስጭት ምትክ ዘፈኖቹን በራፕ እንዳቀነቀናቸው ተናግሯል፡፡

Read 2970 times

Latest from