Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 October 2011 11:05

በ 7 ቢሊኖች አለም የሚድዋይፎችን ሚና ማሳደግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የአለም ህዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ. በጥቅምት 31፣ 2011 ዓ.ም. 7 ቢሊዮን ይደርሳል፡፡ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ይህ ህዝብ ወደዚች አለም የመጣዉ በሚድዋይፎች እገዛ ነዉ፡፡ነገር ግን የእርጉዝ ሴቶችን ፍላጎት ለሟሟላትና ጤናማ ወሊድን ለማረጋገጥ የሚድዉፍሪ አገልግሎቶችን ማስፋፋት ያሻል፡፡ሁሉም እርጉዝ ሴቶች ምርጥና ተግባራዊ ሊሆን የሚችል እንክብካቤና ምክር ሊያገኙ ይገባል፤ ይህ ደግሞ እርግዝናና ወሊድን የሚያግዝ ዉጤታማ መረጃ፣ መግባባት እና ክብር ላይ የተመሰረተ ሂደት ሊሆን ይገባል፡፡

በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠፉ እርጉዝ ሴቶችና ገና የተወለዱ ህፃናት መከላከል በሚቻሉ በሽታዎች ሳቢያ ህይወታቸዉን ያጣሉ፤ ነገርግን ሚድዋይፎች ይህንን ሞት በመከላከል እንዲሁም የአለም ህዝብ ቀጣይነትን በማረጋገጥ በኩል ጉልህ ድርሻ ያበረክታሉ፡፡ የእናቶች ጤናን በማሻሻል ረገድ ሚድዋይፎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡እ.ኤ.አ. በ2005 የወጣዉና ‹‹ለእናቶችና ህፃናት ህይወት ትኩረት መስጠት›› የሚለዉ ሪፓርት እንደሚያመለክተዉ ሚድዋይፎችና የሚድዉፍሪ ሙያ ያላቸዉ ሌሎች የጤና ባለሞያዎች የምእተ አመቱን የልማት ግብ 4 እና 5ን ለማሳካት በሚደረገዉ ጥረት መሰረታዊ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ሚድዋይፎች በእርግዝና ጊዜ፣ በምጥ ወቅት ማንዲሁም ከወሊድ በኃላ ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ይህ ደግሞ የወላዷና የቤተሰቧ አባላትን ከመጥቀም ባሻገር ለመላዉ ህብረተሰብና ለአገሪቱም የሰዉና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ ድርሻን ያበረክታል፡፡
መጪዉን ትዉልድ ከመፍጠር ሂደት ጋር እንደመያያዙ መጠን የአንዲት ሴት ወሊድ በየትኛዉም የአለማችን ክፍል በተስፋ የተሞሉ ቀናት ናቸዉ፡፡ ወሊድ ሚድዋይፎችን በመሳሰሉ የሰለጠኑ የጤና ባለሞያዎች እገዛ በጤና ተቋማት ዉስጥ መከናወኑ እጅግ አስፈላጊ ነዉ ምክንያቱም ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ቀዉሶች በአፋጣኝና ተገቢ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ይቻላልና፡፡ ነገርግን በኢትዮጵያ በሰለጠኑ የጤና ባለሞያዎቸ እገዛ የሚከናወኑ ወሊዶቸ ከ 10 በመቶ አይበልጡም፡፡ በተጨማሪም ለእርጉዝ ሴቶች በተለይ በህብረተሰብ ደረጃ እንክብካቤ ሊሰጡ የሚችሉ በቂ ቁጥር ያላቸዉ ሚድዋይፎች የሉም፤ በአሁኑ ጊዜ ከ 83 ሚሊዮን በላይ ለሚገመተዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ግልጋሎት እየሰጡ ያሉ ሚድዋይፎች ብዛት ከ 3,000 አይበልጥም፤ እ.ኤ.አ. በሰኔ 2011 የወጣዉ የአለም የሚድዉፍሪ ሪፖርት እንደሚያመለክተዉ ቁጥሩ እየጨመረ ያለዉን የአገሪቱን ህዝብ ፍላጎት ለማሟላት እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም. 19,489 የሚሆኑ ሚድዋይፎች ያስፈልጋሉ፡፡ እያንዳንዷ እናትና የወለደችዉ ልጅ ጥራቱን የጠበቀ የሚድዉፍሪ አገልግሎት ያገኙ ዘንድ ቁጥራቸዉ በርከት ያሉ ሚድዋይፎችን ለማሰልጠን ጠንካራ እርምጃዎች መወሰድ ይገባቸዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል እንዲሁም በሞያዉ ለማደግ ያሉ እድሎች አናሳ መሆን ወጣት ሚድዋይፎች በስራ ገበታቸዉ ላይ እንዳይቆዩ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ዉስጥ ሊጠቀስ የሚችል ሲሆን ይህ ደግሞ አገሪቱ በሞያዉ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ቁጥር አናሳ እንዲሆን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አብዘኞቹ ሚድዋይፎች ሌሎች ሞያዎችን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፡፡ ነገርግን የአንዲት ሚድዋይፍ ምስክርነት እንደሚያስረዳዉ የሴቶችን ጤና ለማሻሻል ቁርጠኝነት ገብተዉ በሞያዉ ዉስጥ የቆዩ ሚድዋይፎች ሞያዉ የህሊና እርካታን እንደሚያጎናፅፋቸዉ ይናገራሉ፤ ‹‹እኔ የሚከፈለኝ ገንዘብ እምብዛም አይደለም፤ ነገርግን የምሰራዉን ስራ እወደዋለሁ፤ የእናቶችን ስቃይ ለማስታገስ መቻሌ ደስታን ይሰጠኛል፤ እገዛ ያደረኩላቸዉ ሰዎች የሚሰጡኝ ሀሳብ ስራዬን የበለጠ እንድወድ አድርጎኛል፡፡ በሞያዉ ከተሰማራሁ ጀምሮ ምን ያህል ወሉድ እንዳከናወንኩ በትክክል ባላዉቅም ከ 2,000 በላይ መሆኑን አዉቃለሁ፡፡ እንደ አንድ ሚድዋይፍ የሰለጠንኩ የጤና ባለሞያ፣ አስተማሪ፣ ምክር እንዲሁም እንክብካቤ ሰጪ ነኝ፡፡››
ሚድዋይፎች በርግጥም ሴቶች ተኮርና የሴቶችና ህፃናትን ጤና ለመታደግ ያለመ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሞያዎች ናቸዉ፡፡ በእርግዝናና ወሊድ ወቅት ከሴቶች ጋር ያላቸዉ በጋራ እሴቶች፣ መተማመን፣ ክብር እና ጓደኝነት ላይ የተመሰረተዉ ግንኙነታቸዉ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በሚገባ ይረዳሉ፡፡ ሚድዋይፎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ እየሰሩ ህይወትን ለመታደግ የሚጥሩ ያልተዘመረላቸዉ የህብረተሰባችን ጀግናዎች ናቸዉ፡፡
ወሊድ ለእናትየዉም ሆነ በወሊድ ወቅት እገዛ ለምታደርግላት ሚድዋይፍ እጅግ አስጨናቂና ፈታኝ ሂደት ነዉ፤ ነገርግን ሚድዋይፏ እንዴት ጭንቀቱን እንደምታስወግድና ጤናማ እርግዝናና ወሊድን እንደምታረጋግጥ በሚገባ ታዉቃለች፡፡ ሚድዋይፎች ላይ ኢንቬስት ማድረግ እጅግ ፈታኝ የሆነዉን የእናቶችና ህፃናት ሞትን መፍትሄ በመስጠት በኩል ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ የሚድዊፍሪ ሞያ ለሁለንተናዊ ሰብአዊ መብቶች፣ በተለይም ለሴቶችና ለወለዷቸዉ ልጆች መብት እዉቅና የሚሰጥ ነዉ፤ በዚህ በኩል ሚድዋይፎች ሴቶች የተመረጠ የጤና አገልግሎት ማግኘታቸዉን የማረጋገጥ ሀላፊነት ይኖርባቸዋል ምክንያቱም ይህ ተጨማሪ ሴቶች ወደ ጤና ተቋም በመምጣት ወሊድ እንዲፈፅሙና የጤና ችግሮችን እንዲሁም ሞትን እንዲያስወግዱ ይረዳቸዋልና ነዉ፡፡ የአለም ህዝብ በቅርቡ 7 ሚሊዮን ሊደፍን መሆኑን ስናስብ ሴቶች በማህበረሰብ፣ በህብረተሰብና በአገሪቱ ደረጃ ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ ዘንድ ጤናቸዉ የተጠበቀ መሆን እንደሚገባዉ ማጤን ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ የተረጋጋ፣ ሰላማዊና ምርታማ ማህበረሰብ በመፍጠር በኩል ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡
ሚድዋይፎች የስነ-ተዋልዶ ጤናና መብትን በማራመድ እንዲሁም የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ለሴቶች ተደራሽ የሚሆኑበትን ሁኔታ በማመቻቸት ጥረት ዉስጥ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በተጨማሪም የቤተሰብ እቅድና ከእናት ወደልጅ የቫይረሱን መተላለፍ የሚገቱ ህክምናዎች አቅርቦት ላይ ድርሻ አላቸዉ፡፡ የህዝቡ ቁጥር እየጨመረ በሔደ ቁጥር ሴቶችና ወጣቶች ተጨማሪ የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ያስፈልጓቸዋል፡፡ የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ማዳረስ እ.ኤ.አ. በ2007 የተጨመረ የምእተ አመቱ የልማት ግብ ታርጌት ነዉ፤ ይህንን ታርጌት ለማሳካት ተጨማሪ ሚድዋይፎች ያስፈልጋሉ፤ የአለም ህዝብ በቅርቡ 7 ቢሊዮን ሊሞላ መሆኑን ስናስብ ከሚድዋይፎች ጋር ያለዉን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያሻ መዘንጋት የለብንም፤ እያንዳንዷ ሴትና ጨቅላ ህፃን የሚድዋይፍ እንክብካቤ ይሻሉ፡፡

 

Read 4128 times Last modified on Saturday, 22 October 2011 11:11