Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 October 2011 12:23

የአንጋፋው አርቲስት ልደት በትያትር ምረቃ ተከበረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም አዲስ ትያትር እንዲመርቅ በክብር እንግድነት በተገኘበት ልደቱ ተከበረ፡፡ የአንጋፋው አርቲስት 55ኛ ዓመት ልደት የተከበረው ረቡዕ ጥቅምት 1 ምሽት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ነው፡፡ የዘካርያስ ብርሃኑ ድርሰትና ዝግጅት የሆነው “ዕጣ ፈለግ” ትያትር የክብር እንግዳ አርቲስት ፍቃዱ፤ ለተዋናዮቹና ለትያትሩ እዚህ መድረስ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን በአዘጋጆቹ አቅራቢነት ከሸለመ በኋላ ሳይነገረው የትያትሩ አቅራቢ ሚሙ ፕሮዳክሽን ያዘጋጀለትን ኬክ ቆርሷል፡፡ ዝግጅቱ ሲፈፀም ስለልደቱ አከባበር የጠየቅነው አርቲስቱ፤ አራት ኪሎ አካባቢ መወለዱንና በልጅነቱ ወላጆቹ ያከብሩለት እንደነበር አስታውሶ ያሁኑን ግን ሳያስበው በማዘጋጀት እንዳስደመሙት ነግሮናል፡፡ የትያትሩ ደራሲና አዘጋጅ ዘካርያስ ብርሃኑ በበኩሉ “ባለቀ ሰዓት ትያትሩ ሊከፈት 90 ደቂቃ ሲቀረው በማወቃችን እንጂ እጅግ የምናከብረውን አርቲስት ልደት ሰፋ ባለ ዝግጅት ከዚህ በበለጠ ድምቀት ማክበር እንፈልግ ነበር” ብሏል፡፡

Read 3755 times