Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 October 2011 11:39

ለአበበ ቢቂላ ባለውለታው የስፖርት ማህበር

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ ለ7 አመታት ያህል ከ2ሺህ በላይ ህፃናትና ወጣቶችን በማሰባሰብ በእግር ኳስ፣ በአክሮባት፣ በቅርጫት ኳስ፣ በቦክስ፣ በእጅ ኳስ...የሚሳተፉ 120 ክለቦችን አቋቁመዋል፡፡ ከ2ሺህ አባላት አንድ መቶ የሚደርሱት ሴቶች ነበሩ፡፡ በወጣትነታቸው “ምዕራብ አዲስ አበባ ስፖርት ማህበር”ን መሥርተው የነበሩት አቶ በላቸው ኃይሌ፤ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሳተላይትና ሲስተም ክፍል የቀጥታ ስርጭት ንብረት ክፍል ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አድማሱ ብርሃኑ ሰሙ ከባለታሪኩ ጋር ዊንጌት አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ያደረገው ቆይታ ይህንን ይመስላል፡፡

የትውልድ አካባቢዎ የት ነው?
በሰሜን ሸዋ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ልዩ ስሙ አባቴነህ ተብሎ ከሚጠራው መንደር፤ ሲሆን ሰኔ 5 ቀን 1947 ዓ.ም ነው የተወለድኩት፡፡ በትውልድ መንደሬ እስከ 5ኛ ክፍል ተምሬያለሁ፡፡ በ1957 ዓ.ም አዲስ አበባ ከመጣሁ በኋላ በቀድሞው ወሰንሰገድና ልዑል መኮንን ከተማርኩ በኋላ በጄኔራል ዊንጌት በኤሌክትሪሲቲ በዲፕሎማ ተመርቄያለሁ፡፡
ሕፃናትና ወጣቶችን ለስፖርት ለማሰባሰብ ምክንያትና መነሻ የሆነዎት ምን ነበር?
አዲስ አበባ እንድመጣ ምክንያት የሆነኝ ታላቅ ወንድሜ አቶ ተፈራ መኮንን በወቅቱ ከስፖርት ጋር በተያያዙ ብዙ ተግባራትን ያከናውን ነበር፡፡ የመርካቶን ወወክማ ያቋቋመው አቶ ተፈራ መኮንን ሲሆን፤ የእሱን ምሳሌነት እከተል ነበር፡፡ የምዕራብ አዲስ አበባ ስፖርት ማህበርን እንድመሠርት ይበልጥ ያነሳሳኝ ግን አንድ አሳዛኝ ገጠመኝ ነው፡፡
በወቅቱ እኔ በልዑል መኮንን ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡ ከትምህርት ወጥቼ ወደ ቤቴ ስሄድ ሕፃናት ሽማግሌ ሲሳደቡ፤ ሽማግሌው ሕፃናቱን ሲረግሙ አየሁ፡፡ ምክንያታቸው ልጆቹ የሚጫወቱበትን ብይ ሽማግሌው ሳያውቁ በከዘራቸው በመበተናቸው ነበር፡፡ በዕለቱ ያየሁት ነገር በጣም አሳዘነኝ፡፡ ልጆቹ መዝናኛ ቢኖራቸው ችግሩ አይፈጠርም ነበር ብዬ በማሰቤ፣ የስፖርት ክለቦቹን ለማቋቋም ተነስቼ ተሳካልኝ፡፡
የክለቦቹ አመሠራረት ሂደት ምን ይመስል ነበር?
በወቅቱ ተማሪ ብሆንም ከወንድሜ ከአቶ ተፈራ መኮንን ጋር መሳለሚያ አካባቢ በሚገኘው ቀስተ ደመና ትምህርት ቤትም እሰራ ነበር፡፡ በተለያየ ስፖርታዊ ውድድሮች መሳተፍ የምትፈልጉ መጥታችሁ ተመዝገቡ የሚል ማስታወቂያ ጽፌ በቀስተ ደመና ትምህርት ቤታችን በር ላይ ለጠፍኩ፡፡ ብዙ ወጣቶች መጥተው ሲመዘገቡ ዋንጫ አዘጋጅቼ ማወዳደር ጀመርኩ፡፡ በእግር ኳስ የተጀመረው ውድድር እየሰፋ ሄዶ ብዙ ክለቦች እንዲቋቋሙ ምክንያት ሆነ፡፡
ውድድሮቹን በትምህርት ቤቶች፣ በፈጥኖ ደራሽ ግቢና መሳለሚያ አካባቢ በሚገኘው ኳስ ሜዳ ነበር የምናካሂደው፡፡ የምንሰራው ሥራ የምዕራብ አዲስ አበባ ዞን ሕፃናትና ወጣቶችን ብቻ ሳይሆን የብዙ አካላትን ትኩረት እየሳበ መጣ፡፡ የፈጥኖ ደራሽ ግቢ አዛዥ ጄኔራል ገ/እግዚአብሔር ሜዳቸውን እንድንጠቀምበት ከመፍቀዳቸውም በተጨማሪ መኪና የሚያቀርቡልን ጊዜ ነበር፡፡
የስፖርት ፌዴሬሽን 20 ወጣቶችን በዳኝነት አሰልጥኖ አስመረቀልን፡፡ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሥራችንን በቅርበት ይከታተሉ ነበር፡፡ ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ በጋዜጣው ላይ በየጊዜው ስለ ምዕራብ አዲስ አበባ ስፖርት ማህበር ይጽፋል፡፡ ይንበርበሩ ምትኬ በሬዲዮ ብዙ ዘገባ ሰርቷል፡፡ የመሳለሚያና የመርካቶ አካባቢ ነጋዴዎችና ታዋቂ ሰዎች በኮሚቴው ውስጥ ገብተው በተለያየ መልኩ ያግዙን ጀመር፡፡
ለስፖርት ማህበሩ ሴቶችን ለመመልመል ያነሳሳዎት ገጠመኝ ምን ነበር?
በ1962 ዓ.ም የኬኒያ አትሌቶች ለውድድር ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡ ቡድኑ ወንዶችን ብቻ ሳይሆን ሴቶችንም አቅፎ ነበር፡፡ በዘመኑ ሴት ኢትዮጵያዊያን ተወዳዳሪዎች ባለመኖራቸው ምክንያት ኬኒያውያኑ ቅሬታቸውን አቅርበው ዜናውን ጋዜጦች ላይ አነበብኩ፡፡ ከዚያ በኋላ በመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች በመዞር ለዳይሬክተሮች ጉዳዩን በማሳወቅ፣ ሴቶችን በማበረታታት በምዕራብ አዲስ አበባ ስፖርት ማህበር ክለቦች ውስጥ እየገቡ መሳተፍ በመጀመራቸው ለውጥ መታየት ጀመረ፡፡
ስፖርት ማህበሩ በሕጋዊነት የተመዘገበበት ዕውቅና ነበረው?
የማህበሩ ቢሮ ይገኝ የነበረው በቀስተ ደመና ትምህርት ቤት ግቢ ነበር፡፡ ከአባላቱ የሚሰበስብ ምንም ገቢ አልነበረም፡፡ ለማህበሩ እንቅስቃሴ በጐ አድራጊዎች ገንዘብ መለገስ ሲጀምሩ ነበር ማህበሩን በበላይነት የሚመራ ኮሚቴ ያዋቀርነው፡፡ በኮሚቴው ውስጥ መኮንን ተፈራ፣ ሞላ በዳኔ፣ በርሲሳ በዳዳ፣ ጥላሁን ደቦጭ እና በአካባቢው የሚገኙ ትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች ነበሩበት፡፡
ከስፖርት ኮሚሽን ከአቶ ይድነቃቸው ተሰማ የተሰጠን ፈቃድ ነበር፡፡ አቶ ይድነቃቸው በምዕራብ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአራቱም አቅጣጫ የስፖርት ማህበራት እንዲቋቋሙ መመሪያ ሰጥተው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በሰሜን አዲስ አበባ ቀጨኔ ጉቶ ሜዳ አካባቢ አቶ ዳምጠው ሀብቴ ሕፃናትና ወጣቶች የሚሳተፉበት የስፖርት ማህበር አቋቁመዋል፡፡
የምዕራብ አዲስ አበባ ስፖርት ማህበር በዚህ መልኩ ለሌሎችም ምሳሌ መሆን በመቻሉ፣ ከስፖርት ኮሚሽንም ዕውቅና ከማግኘቱም ባሻገር ከደህንነት ቢሮ የሰጠን ፈቃድ ነበረን፡፡ የሕዝባዊ ኑሮ ዕድገት ምክትል ሚኒስትር አቶ አበራ ሞልቶት፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህና ቀኛዝማች አማኑኤል ሙላት የማህበሩ የበላይ ጠባቂ ሆነዋል፡፡
ከመንግሥት ያገኛችሁት እገዛ ምን ነበር?
የወጣቶቹ የስፖርት እንቅስቃሴና የአባላቱም ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ውድድር የምናካሂድበት ቦታ ችግር ሲያስጨንቀን፣ ራስ ኃይሉ ሜዳ እንዲሰጠን ጠየኩኝ፡፡ የመንግሥት ምላሽ ፈጣን ነበር፡፡ ከንቲባው ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህ ሜዳው ድረስ ሄደው አይተው ነው ይሰጣቸው ብለው የውሰኑት፤ ይህንኑ እንዲያስፈጽሙልን የማዘጋጃ ቤት የፓርክ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ልዑልሰገድን መደቡልን፡፡ ቦታው በማን ስም ይመዝገብ ሲባል ባለቤትነቱ የማህበር ሆኖ ስያሜው ለአገሩ በስፖርቱ ዘርፍ ታላቅ ታሪክ ባስመዘገበው በሻምበል አበበ ቢቂላ ሥም ይሁን አልኩ፡፡ ከዚያ በኋላ የከንቲባው ጽሕፈት ቤት በራስ ኃይሉ ሜዳ ላይ ስለሚሰራው የስፖርት ማዕከል ጥናቱን አሜሪካን ልኮ ነበር ያሰራው፡፡
አበበ ቢቂላ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ካሸነፈ በኋላ ጃፓኖች አዲስ አበባ ውስጥ በሥሙ ስታዲየም ሊሰሩለት ጥያቄ አቅርበው ነበር የሚባለውስ
የራስ ኃይሉን ሜዳ ለእኛ የስፖርት ማህበር እንዲሰጥ እኔ ከመጠየቄ በፊት ቦታው ላይ ሊሰራ የታቀደ ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ለእኛ ከተፈቀደና በሻምበል አበበ ቢቂላ ሥም ይሁን የሚለውም ይሁንታ ካገኘ በኋላ ለተግባራዊነት ስንንቀሳቀስ ብዙ ችግር ገጥሞናል፡፡ አንደኛው የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ነበር፡፡ በራስ ኃይሉ ሜዳ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በጣሊያን ጊዜ ከ4 ኪሎ ተፈናቅለው እዚያ እንዲሰፍሩ የተደረጉ ስለነበሩ ቦታው ለእኛ ሲፈቀድ ዳግመኛ ልንፈናቀል ነው በሚል ከእኛ ጋር የተጋጩበት ጊዜ ነበር፡፡
ከቦታው ጋር በተያያዘ የገጠመን ሌላው ችግር ቦታውን እንዲያስረክቡን የታዘዙት የማዘጋጃ ቤት ሠራተኞች መሬቱን ለሚያስተካክሉ ግሬደሮች ነዳጅ መግዣ፣ ለሠራተኞቹም የውሎ አበል ካልከፈላችሁን በሚል ለሥራው መጓተትና አለመቀጠል ምክንያት ሆኑብን፡፡ የገጠመንን ችግር ለመቅረፍ ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ ብዙ ደክሟል፡፡ በዚህ መሐል አብዮቱ ፈነዳ፡፡ ደርግም በግል የሚንቀሳቀሱ የስፖርት ማህበራት ይቁሙ ብሎ አገደን፡፡
በንጉሥ ኃይለሥላሴ የወርቅ ሣንቲም መሸለምዎት ይነገራል
በስፖርት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ አገልግሎትና በማሕበራዊ ጉዳዮች በስፋት እንቀሳቀሳለሁ፡፡ የቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አባልና 3ኛ ፕሬዚዳንት ነበርኩ፡፡ የራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት ከአፄ ኃይለሥላሴና ከእቴጌ መነን ጋር ስለተያያዘ “የቤተመንግሥት ታቦት ነው” ይባላል፡፡ ንጉሡ ለንግሥ በየዓመቱ ይመጡ ነበር፡፡ በሰንበት ትምህርት ቤት ላገለገልንበት እንደምስጋና ነው የወርቅ ሣንቲሙን የሰጡን፡፡
ከተለያዩ አካላት 31 ሠርተፍኬቶችን እንደተበረከተልዎ ሰምቼአለሁ፡፡ ከነዚህ መሐል ሁለቱን መርጠው ከየትና ለምን እንደተሰጥዎት ይንገሩኝ…
በስፖርት፣ በአካባቢ ጥበቃና በጽዳት ላይ ላበረከትኩት አስተዋጽዖ ከከንቲባ ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህ የተሰጠኝ የወርቅ ሜዳሊያና ሠርተፍኬት አንዱ ነው፡፡ ሌላው በመርካቶ ወወክማ ፊልም አሳይ በነበረበት ወቅት፣ ለጥረትና ትጋቴ ከአሜሪካ ቤተመፃሕፍት የተሰጠኝ ሠርተፍኬት የተመሰገንኩበት ነው፡፡
በ1992 ለፓርላማ ተወዳድረዋል፡፡ ማንን ወክለው ነው?
በግል ነበር የተወዳደርኩት፡፡ ለጥቂት ነው የተሸነፍኩት፡፡
በምን እናጠቃልል?
ባለትዳርና የ8 ልጆች አባት ነኝ፡፡ አንዷ ልጃችን በቅርቡ በሞት ተለይታናለች፡፡ በሕይወት ዘመኔ ጊዜዬን በአግባቡ ተጠቅሜበታለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ በስፖርት፣ በመንፈሳዊ አገልግሎት፣ በዕድሮች፣ በቀበሌ፣ በጤና ጉዳይ፣ በብዙ የማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ተሳትፎ አለኝ፡፡ ሰውን አክብሬ በሰዎችም ተከብሬ፤ ለአገሬና ለሕዝብ የምችለውን ሰርቻለሁ፡፡ አሁንም በመሥራት ላይ እገኛለሁ፡፡ ለሕዝቡ ጤናና ፍቅር፤ ለአገር ሠላም እመኛለሁ፡፡

Read 4617 times Last modified on Saturday, 15 October 2011 11:56