Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 October 2011 10:18

“ቤይሩት” የተሰኘ ፊልም ተሰራ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሊባኖስ የምትኖረው ራሄል ዘገየ  “ቤይሩት” በሚል ርዕስ በኢትዮጵያውያን የስደት ኑሮ ላይ ያተኮረ ፊልም እየሰራች መሆኑን ከታድያስ ድረ ገፅ ጋር ባደረገችው ቃለምምልስ ተናገረች፡፡ ፊልሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሚደርስባቸው የጉልበት ብዝበዛ፣ ፆታዊና ሰብአዊ  ጥቃቶችና ሌሎች በደሎች ዙርያ ያውጠነጥናል ብላለች፡፡ኢትዮጵያውያን በመካከለኛው ምስራቅ  በሚደርስባቸው በደል ልቤ ይቃጠላል ያለችው ራሄል፤ በሃያ ዓመቷ በሊባኖስ በቤት ሰራተኛነት ለመስራት ከአገሯ መሰደዷን ትናገራለች፡፡

ፊልሙ በቤት ሰራተኛነት በሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ህይወት ላይ እንደሚያተኩር የገለፀችው ራሄል፤ በበቤይሩት ለአስር ዓመት ስትሰራ የታዘበችውን በፊልሟ ውስጥ ማካተቷን ተናግራለች፡፡ ፊልሙ በተለይ በሊባኖስ በቤት ሰራተኞች ህይወት ዙሪያ በይፋ ስለማይገለፁ አሳሳቢ ጉዳዮችም እንደሚያሳይ ገልፃለች፡፡
በአዲስ አበባ በፈረንሳይ ለጋሲዮን ተወልዳ ያደገችው ራሄል፤ “ቤይሩት” የተባለውን የፊልም ስክሪፕት ለማዘጋጀት ዘጠኝ ዓመት እንደወሰደባት፣ ቀረፃውንም በሁለት ዓመት እንዳጠናቀቀች ለ “ታድያስ” ተናግራለች፡፡

 

Read 3188 times Last modified on Saturday, 08 October 2011 10:20