Print this page
Saturday, 08 October 2011 09:18

የሥርዓቱ አንዳንድ ስንጥቆች

Written by  አበባየሁ ለገሠ
Rate this item
(0 votes)

በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ የሚገኙት የ|ድራማ´ አይነቶች በርካታ ናቸው፡፡ |ድራማ´ ተባለ እንጂ የ|ፊልሙ ዘውግ´ በየመስኩ የሚታወቅ ነው፡፡ በአገር፣ በማህበረሰብ፣ በቤተሰብ፣ በግለሰብ ደረጃ እየቋጠረ ያለ የሚመስለው የጥፋት መንገድ አመራር አንስቶ ታች ድረስ ምን እየተሰራ እንደሆነ ግልፅ እያደረገው የመጣ ይመስላል፡፡
የሕገ ወጥ ድርጊቶች ተፈፃሚነት መደጋገም በተለይ ወንጀሎቹ የተፈፀሙባቸው ግለሰቦች ሲሆኑ ነገሮች በምን መልኩ እየተጓዙ እንደሆነ፣ በማን ቀጥተኛ ትዕዛዝ እየተከናወኑ ስለመሆኑ ተጨባጭ ቅርፅ እየያዙ ይመጣሉ፡፡

መሪና ተመሪ
እንኳን አገር ራስን መምራትም ሊከብድ ይችላል፡፡ አገር የመምራት ችሎታ፣ ልምድ፣ ባህርይ፣ ሥነ-ምግባር፣ ለአዲስ ጤናማ አስተሳሰብና ቴክኖሎጂ ቅርብነት … ያለነዚህ ለውጥ አይታሰብም፡፡
በሰፊ አገር ውስጥ ሆደ ሰፊ የሚኮኑባቸው ጉዳዮች እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ የመሪዎች ባህርይ የሚሻከረው ሌሎች ከሚፈጥሩባቸው |ያልተገባ ድርጊት´ ብቻ ሳይሆን የራሳቸው አስተሳሰብና አቋም ጭምር ነው፡፡ በጥቂት ነገሮች ሆድ የሚብሳቸው መሪዎች አሉ፡፡ የትየለሌ ዕዳዎችን የሚሸከሙም ይኖራሉ፡፡
የመሪ መሳሳት በአገርና በማህበረሰብ ላይ ሲሆን የከፋ ይሆናል፡፡ ግለሰቦችን ማዕከል ያደረገ ሲሆን፣ በተለይ አንዳንድ ወሬና መረጃ አቀባዮች ያሴሩት የት ድረስ እንደሆነ ሳያጤኑ፣ ያልታተመ ልቦለድ፣ ታርሞ ያልተጠናቀቀ፣ ማተሚያ ቤት ያልገባ፣ ከመግባቱ በፊትም የአገሪቱን ሕግ ተከትሎ፣ እያንዳንዱን ደረጃ አልፎ ለፍትሕ አካል ያልቀረበን ሥራ መነሻ በማድረግ፣ |ወንጀልነት´ ካለው የትኛው ሃሣብ እንደሆነም ለመለየት ያልተቻለን ልቦለድ በሰበብነት ተደግፎ ግለሰብ ላይ |መወሰን´ የስልጣን አጋጣሚ እና ዕድል በዚህ አገር የት ድረስ የሚያስኬድ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ፖለቲካዊ ውሣኔ ለሰላም፣ ለወዳጅነት፣ ለልማት፣ ለገንቢ ነፃነት... መሆኑ ቀርቶ የተስፋ መርገብ መኖሩን ነው የሚያጭረው፡፡
ከአምስት አመታት በፊት የተፃፈን ሥራ መነሻ በማድረግ ረiም መንገድ መሄዱም ሥርዓቱ ለሕግና ሥርዓት፣ ለመስመር ያለውን የአቋም መዋዠቅ ያመለክታል፡፡ እንዲህ አይነቱ ውል አልባ ድርጊት እንዲፈፀም የሚፈልጉ የተለያዩ ግለሰቦችም አሉ፡፡ የፍላጐታቸው የጥፋት ጫፍም ምን እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ እነርሱ ያመቻቹት አልያም ለነርሱ የተመቸው ይህ አስገራሚ የተፅዕኖ ዝንባሌ ወደ ተለያዩ ምንጮች ሊያመራ ይችላል፡፡
የተወሠኑ የኢህአዴግ የደህንነት አባላት በየመስሪያ ቤቱ እየዞሩ ምንም አይነት ሥራ እንዳልሠራ ውስጥ ለውስጥ የሚሯሯጡት፣ ስልክ እየጠለፉ በግኑኝነቶች ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚሞክሩት፣ የቅርብ ወዳጅነት ያላቸውን ሰዎች ጊዜያዊ የፖለቲካ ሥልጣንን በመጠቀም ለመደለል መሞከራቸውን ማወቅ ከሚታወቀው ሕግ ውጭ ድብቅ |የሚፈፀም ሕግ´ መኖሩን ይገልፃል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን አለመሆን፣ ለምን የግዴታ ውሣኔ ይሆናል? በተለይ ኢህአዴግ በትግሉ ወቅት ፍቃደኝነትን ተከትሎ አባል መሆን ያልፈለጉትን ቢያንስ ድንበር ድረስ በመሸኘት ያሻግር እንደነበር ይታወቃል፡፡ በሲቪል አስተዳደር ውስጥ ግን የግዳጅ ምልመላ ያካሂዳል፡፡
አንድን ግለሠብም ሆነ ብዙሃኑን በኑሮው ላይ ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ጫና በመፍጠር የፓርቲ አባል እንዲሆን በማድረግ ምን አይነት መፍትሔ ማምጣት እንደሚቻል መገመት አይከብድም፡፡ ውጤቱን ለማወቅ የተለየ ጥረት አያስፈልግም፡፡
አቋም በጐዳና ላይ ሐሜት መጥበቅና መላላት አይያዝም፡፡ ሥልጣንም በበቀል እና ዕልህ አይናፈቅም፡፡ ሲይዙትም ይህ ሊታሰብ አይገባውም፡፡
መቼም ቢሆን አባል ያለ መሆን መብትን በማንኛውም ተፅዕኖ ለመቀልበስ መሞከር የመጨቆን ልምድ ውጤት ነው፡፡ በተለይም የጥላቻ ፖለቲካን ማራባት መድረሻው ይታወቃል፡፡ ማንኛውንም ዓይነት |ስም የመስጠት´ ጥረትም በዚህ ጉዳይ ላይ ለውጥ አያመጣም፡፡
ጠቅላይ ማኒስትሩ ሌሎች ምክንያቶች ቢኖራቸው እንኳ ከመንግስት አመራር፣ ጤናማ ኅብረተሰብን ከመገንባት አንፃር፣ አንድን ወይም የተወሠኑ የተመረጡ ሰላማዊ ግለሰቦችን አላማ ያደረገ ዕድሜን፣ ዕውቀትን፣ ልምድን፣ ኃላፊነትን፣ መጪውን ጊዜ ያላገናዘበ ግላዊ ጐጂ |ትዕዛዝ´ ይሠጣሉ ብሎ መገመት ይከብድ ነበር፡፡ ይኹንና ሆኗል፡፡ አንዳዴም ሊታዘዝ የማይገባውን ማዘዝ፣ ሌሎች ጥቂቶችም የተሳተፉበት መሆኑ ሲጠቆም ምንም ነገር የሌለ ለማስመሰል መሞከር አንድ ሕገ-ወጥ አቋም መኖሩን ይኖራል፡፡
የምንፈልገውን እንወደዋለን፣ እናከብረዋለን፣ የሃሣብና የአቋም አንድነት ይኖረን እንደሆን መርምረን እንወስናለን፣ ለማንኛውም ጤነኛ ተልዕኮና ኃላፊነት ፍላጐትና ውሣኔ ካለ ይህን እናጤናለን፡ ቀጥሎም ወደ ተመሳሳይ ጐዳና እንጋብዛለን፡፡
ነገር ግን የአላማ፣ የፍላጐትና የሚሄዱበትን መንገድ ምርጫ ልዩነት ካለ፣ መተው ነው መፍትሔው፡፡ ጤናማ አእምሮ ያለው ሰው ይህን ነው የሚወስነው፡፡ የተሻሉ ሃሣቦች መቀነሳቸውን ወደሚያመለክቱት የሥነ ምግባር ዝቅጠት፣ ጉንተላ፣ ሐሜት፣ በየመስሪያ ቤቱ እየዞሩ የሥራ ዋስትናን ማሳጣት፣ የስልክ ጠለፋን ለአሉታዊ ተልዕኮዎች ማዋል፣ ሥልጣንን በጋሻነትና በጦርነት እየተጠቀሙ የበታች ሠራተኞች የማሰብ ችሎታ እንኳ የማይፈቅዷቸውን ድርጊቶች ማስፈፀም፣ ለራስም ለሌሎችም ማረፊያን ማሳጣት ነው፡፡
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጥፋት ሲፈፅም በሕግ መታረም የለበትም የሚል አይኖርም፡፡ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ ይሁን እንጂ! የሕግ ተልዕኮ ያሰቡት ባለመሳካቱ ብቻ |ለመበቀያነት´ የሚመዘዝ ስለት መሆን የለበትም፡፡
በጤናማውም ሆነ በህገ-ወጡ መንገድ ጥፋት ያልተገኘባቸውን ግለሰቦች |ከዕለታት አንድ ቀን እንዲያጠፉ ማድረግ አለብን´ በሚል ይህን ዕውን ለማድረግ የሚሯሯጡ መኖራቸው፣ ዘንባባ አንጥፎ፣ ምንጣፍ ዘርግቶ በናፍቆት መጣባበቅ ወይም በሁሉም አቅጣጫ ወደዚህ ጥፋት እንዲገባ መረባረብ የጤንነት ካለመሆኑም በላይ |ያልተፃፈ ሕግን´ የማስከበር ያህል ነው፡፡ እንዴት ከዚያ ሁሉ መሀል ሚዛን የያዙና አቅጣጫ የሚያስጠብቁ ሰዎች ይጠፋሉ ያሰኛል፡፡ ከዚህ አንፃር የአገሪቱንም ሆነ የሰማኒያ ስንት ሚሊዮን ሕዝብ ዕጣ ፈንታ በግልም ሆነ በቡድን ደረጃ ሰለሚኖረው አለኝታነት በምን እርግጠኝነት መናገር ይቻላል?
ግብረ ሰዶማዊነትን መቃወም...
ግብረ ሰዶማዊነትን መቃወም የድርጊቱን ፈፃሚዎች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወም አይደለም፡፡ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ሊለወጡ እንደሚችሉ እና የተለወጡም እንዳሉ ይገልፃሉ፡፡ ሕግን አለማክበር የሌሎችን መብት መጣስ ነው፡፡ ሕግን አለማስከበር የሌሎች መብት እንዲጣስ ማመቻቸት ነው፡፡ ተሳስቶ ሌሎችን ለማሳካት |መስራት´ ትክክል ካለመሆኑም በላይ የዘመናት ፀፀትን ያሸምታል፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት፣ የአገሪቱ የቤተሰብ ሕጐች፣ የወንጀል ሕጉ ለዚህ ድርጊት ዕውቅና አይሰጡም፡፡ ከ1949 ዓ.ም ጀምሮ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ በአንቀፅ 600 እና ሌሎች ተመሳሳይ ድንጋጌዎች መሠረት በወንጀልነት መዝግቦታል፡፡ የ1997 ዓ.ም የተሻሻለው የወንጀል ሕግ በበኩሉ፤ በአንቀፅ 629 እና ተከታይ ድንጋጌዎቹ መሠረት ቅጣቱ እስከ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ይደርሣል፡፡
ዛሬም ቢሆን የሕግ ሽፋኑ በቂ እንዳልሆነ በተለያየ መንገድ እየተጠቆመ ነው፡፡ የድርጊቱ ሂደት እየተወሳሰበ እንደመጣ በይፋም ሆነ በውስጥ የሚያመለክቱ ጥቂት አይደሉም፡፡ ለዚህም የውጭ ዜጐች ሚና ቀላል ግምት አይሰጠውም፡፡ ይህ የሌሎችን መብት ተጋፍቶ የሚገኝ ጥፋት በወንዶች ብቻ ሳይሆን በሴቶች መካከልም ወደዚህ ድርጊት እንዲሳቡ ጥረት የሚያደርጉ መሆናቸውን የሚጠቁሙ ቢኖሩም አድማጭና መፍትሔ ሰጪዎች የጉዳቱን ስፋትና እያደረሰ ያለውን ትውልድን የመበተን አደጋ እና ፈተናውን ለመቀነስ ያልተወሰነው ለምንድን ነው? ዝምታው ያስፈለገው ድርጊቱ የሚወገዝና የጤና እክል መሆኑን ለማገናዘብ ጊዜና ፍቃደኝነቱ ጠፍቶ ነው? ወይንስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለዘመናት የተሸከማቸው የኑሮ እባጮች እንዲህ ዓይነቱን ሁኔታ ለመመልከት አላስቻለንም?     
በአንድ በኩል ገለባ ምክንያቶችን በማዘጋጀት ለዚህ ድርጊት ቲፎዞ ለማብዛት የሚከናወን ጨዋታ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይህን ለማሳካት በሚመስል መንገድ ከሥራ ገበታቸው የሚሠናበቱ፣ በኑሮ ውሏቸው በርካታ እንቅፋቶች እንዲገጥማቸው የሚደረጉ፣ ይህን ድርጊት በመቃወማቸውና መቼም የሚዋጉት ከመሆኑ አንፃር እንዲህ አይነት አቋም ያላቸውን ሰዎች በተለያዩ መንገዶች አስቂኝ ሰበቦችን በማደርጀት ለማዳከም መድከም እንዴት መፍትሔ ሊሆን ይችላል? ይህ ድርጊት የህክምና ክትትል ጉዳይ ስለመሆኑ የሚበዙት ይስማሙበታል፡፡ ያልገቡትን ማዳን ግዴታ ነው፡፡ የገቡት እንዲወጡ ማድረግም ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን የሕግና የፍትሕ ጉዳይ ይሆናል፡፡
ኡጋንዳ የዚህ ድርጊት እየጨመረ መምጣት አሳስቧት፣ የዜጐቿን እጣ ፈንታ አርቃ በማሰብ ራሱን የቻለ ሕግ ባለፈው 2003 ዓ.ም አዘጋጅታ ነበር፡፡ እንዲያውም የመጨረሻው ቅጣት የሞት ፍርድ ሆኖ በኋላ በርካታ አስተያየቶች ቀርበው ወደ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀየር መድረጉን ከመገናኛ ብዙሃን ተደምጧል፡፡
መንግስት፤ ኅብረተሰቡ ሰላማዊና ጤናማ ሕይወት እንዲኖር ማድረግ ያለበትን ጥንቃቄና እርምጃ መውሠድ ይኖርበታል፡፡ ለለውጥ የሚዘጋጁ ካሉ ደግሞ በራስ ወጪ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማገዝ ይኖርበታል፡፡ ለድርድር የሚቀርቡትንና የማይቀርቡትን ለይቶ ማወቅ አንዱ የመንግስት ኃላፊነት ነው፡፡ ለሕግ ተገዢ መሆን ወይም ያለመሆን ውሣኔ ለየግለሰቡ የሚተው ቢሆንም የመንግስትና የኅብረተሰቡ ኃላፊነት ግን ግልፅና ቀጥተኛ ነው፡፡ ከፖለቲካ አመለካከት ጋር የሚያያዝ መሆን የለበትም፡፡ ምክንያቱም በዚህ የሚድንም፣ የምትድንም አገር የሉም፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ!ወደዚህ ድርጊት ለመሣብ የሚደረጉ ተፅዕኖ መፍጠሪያ መንገዶች በርካታ ናቸው፡፡ |ሽብርተኝነት´ ትርጉሙ ወጥነት የሌለውና ለተለያዩ የተሳሳቱ ተፅዕኖዎች ዕድል የሚሰጥ ቢሆንም ተመሳሳዩን በጉያ ይዞ መገኘት ምን ሊባል ነው? ስልታዊ ፍቃደኝነትን በመስጠት ወንጀልን ማስፋፋት የስልጣን መከታነት ኖሮት ከሆነ፣ ኅብረተሰቡ ለህልውናው መቆም ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
ተቋማት ምን እያደረጉ ነው?
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ምን እየሰራ ነው? አናውቅም እንዳይሉን! እንዲያውም ይህ ተቋም በሌሎች ዘርፎች ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ ተመስጋኝነቱ ጨምሯል፡፡ በዚህ ጉዳይስ?
የደህንነት ተቋማት በዚህ ጉዳይ ምን እየሰሩ ነው? የሚደነገገው ይህን ማካተት የለበትም? አገሪቱ ይህን ጥፋት ተሸክማ መድረስ የሚገባት ከፍታ ላይ ትደርሳለች? የፍትሕ አካላት በተለይ አቃቤ ሕግ፣ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ እና ማረሚያ ቤቶች ከአደጋው ስፋት መጨመር ጋር የሚመጣጠን ሥራ ነው እየሰሩ ያሉት? ሁሉም የየራሳቸው ድርሻ ቢኖራቸውም በጥምረት ሊያስገኙ የሚችሉት ውጤት ግን ይታወቃል፡፡ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን በዚህ ጉዳይ ምንም ሲሉ አይታዩም፡፡ ለምን? የተወሰኑት ነካ አድርገው ያልፋሉ፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪiን፣ የሬዲዮ ፕሮግራሞች፣ በተለይ ጋዜጦች      ለምን ዝም አላቸው? ስለ ጉዳዩ  ስለማያውቁ ነው? የተወሰኑ የሚዲያ ሽፋን የሰጡ የሬዲዮ ፕሮግራም፣ የጋዜጦች እና መፅሔቶች አምዶች ይታወሳሉ፡፡ ግን ከበቂ በታች ናቸው፡፡ የረiም ጊዜ ተከታታይ ዕቅድ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ ያለበለዚያ ለውጥ የለውም፡፡ ይሄን ድርጊት የሚደግፍ እንኳ ቢኖር ወጥቶ ይከራከር!
የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለዚህ ጥፋት አቋማቸውን በይፋ ይግለፁ፡፡ የኢህአዴግ ፓርቲዎች እና ግንባሩ ምን ይላሉ? በእርግጥ የአገሪቱ ህገ-መንግስትና ዝርዝር ህጐች ከያዙት አቋም የሚለይ ሀሣብ ይኖራቸዋል ተብሎ አይጠረጠርም፡፡ ለማንኛውም ይናገሩ!
የሙያ ማህበራት በተለይ ሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሠሩ ለምን ይደበቃሉ - በዚህ ጉዳይ?
ታዋቂ ግለሠቦች፣ አርቲስቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሚሊተሪ ባለሙያዎች፣ የደህንነት ባለሙያዎች፣ የበጐ አድራጐትና ማህበራት ድርጅቶች፣ የፍትሕ አካላት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆች፣ ትምህርት ቤቶች... የሚገኙበት ጠንካራ ወርክሾፕ ነገር በአጭር ጊዜ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ በጤና፣ በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በሚዲያ፣ ፍትሕ እና ሕግ ላይ የሚሠሩ ስለ ጉዳዩ በቂ እውቀት ያላቸው ጥናት ቢያቀርቡና ተጨማሪ የመትሔ ሃሣቦች ቢነሰዘሩ መልካም ነው፡፡
ሙያዊ ነፃነት
ሙያዊ ነፃነት ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብና አተገባበር ያላቸው አስተማማኝ መሠረትና አማራጮች ያሉ በመሆናቸው፣ ሙያዊ ነፃነቱን ለማስከበር የሚሞክር ይሄን ያህል እንቅፋቶች አይገጥሙትም፡፡
ሙያውን ማክበርና ማስከበር፣ የሙያውን ውድቀት ኢላማ ያደረገ ድርድር፣ ሙያዊ ምላሽ አለመስጠት፣ በሙያው ክበብ ውስጥ መታየትና መታረም ያለበትን አለመፈፀም፣ ሙያዊ ውሣኔ አለመወሰን፣ ሙያዊ ኃላፊነትን አለማስደፈር፣ በመጨረሻም የሙያው ነፃነት በነዚህና በተመሣሣይ ስልታዊ ጫናዎች ሲሸረሸር ሥራን መልቀቅ ሙያዊ ነፃነትን ለማስከበር አንዱ አማራu ነው፡፡ ይኹንና በዲሞክራሲና ልማት ድህነት ውስጥ ባሉ አገራት ይህ ዕርምጃ ፈታኝ ሊሆን ይችላል፡፡
ሚዲያ መወጣት ያለበትን ኃላፊነት እንዳይወጣ ማድረግ፣ ዳኛ መወሰን የሌለበትን እንዲወስን፣ አቃቤ ሕግ መክሰሰ የሌለበትን እንዲከስ፣ የጤና ባለሙያ ከሙያው መነፅር ውጪ እንዲመለከት ማድረግ፣ ደህንነት የመጀመሪያና የመጨረሻ ኃላፊነቱን እንዳይወጣ ማወሳሰብ፣ የራስ ጉድፍ በረiም ጊዜ የሃሰት ዘመቻ የሌላው ይሆናል ብሎ መትጋት፣ የመሪነትን ሁሉን አቀፍ ሚና መጫወት አለመፈለግ፣ የበርካታ የልማትና የዲሞክራሲ ዕጦት ያለባቸው አገራት |ነፀብራቆች´ ናቸው፡፡ በሂደት መልዕክታቸውንም ግልፅ ያደርግዋል፡፡
የብሔር እና የአመለካከት ልዩነት
በርካታ ችግሮቻችን በአመለካከት ጉድለትና ድንበራችንን ባለማወቅ ጥልቀቶች የመጡ ናቸው ማለት ይቻላል፡፣ ጠላትነትን የመስራትና የማባዛት ባህሪያችንም ከነዚህ የራስ ክፍተቶች የሚመነጩ ናቸው፡፡ በተለይ አድርባይነት ለዚህ ክፍተት በእርሾነት ሲያገለግል ተመልክተናል፡፡
አመለካከታችን የፈቀድነው ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ በተለያዩ ጥረቶች እንዲፈጠሩ፣ እንዲቆሙ፣ እንዲዳብሩ፣ ስር እንዲሰዱ የሚደረጉ፣ ለዚህ የጥፋትም ይሁን የልማት ተልዕኮ ሳይታክቱ የሚሠሩ ሰዎችም ውጤት ነው፡፡ ይህን ተረድቶ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ቢሆንም ፊት ለፊት እየተፈፀሙ ያሉትን ጥፋቶች ወይም ወንጀሎች ያልተመለከቱና የማይውቁ መምሰል በተለይ ከመንግስት የሚጠበቅ አልነበረም፤ አይደለም፡፡ የብሔር ልዩነትን በማንቀሳቀስ የሚታወቅ መንግስት የአመለካከት ልዩነትን ለምን ይፈራል? የአመለካከት ልዩነትን በመደፍጠጥ የብሔር ልዩነትን ብቻ ማጠናከርስ የት ያደርሳል? የብሔር ልዩነትን በመነሻነት ወስዶ ውስጣዊ አፍራሽ ተፅዕኖ ለመፍጠርስ ለምን ይሞከራል? የሃሣብ ልዩነትን መግለፅ ስህተት ከሆነ ከሕጉ ነው? ከአስፈፃሚው ነው? ከገላጩ ነው? የሚሉት መታየት ያለባቸው በሕጉ ወይስ በብሔሩ? በእርግጥ ልዩነቶች ሁሉ ይከበራሉ፣ ስፍራ ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም፡፡ ለራስም ሆነ በአጠቃላይ ለኅብረተሰቡ አደገኛ የሆኑ ልዩነቶች አሉ፡፡ ከፖለቲካ፣ ከጤና፣ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ከማህበራዊ ሕይወት፣ ከህፃናትና ወጣቶች ደህንነት አንፃር ቢሰሉ መፍጠር የተፈለገው የልዩነት መንገድ በፍፁም ሊፈቀድ የማይገባው ሊሆን ይችላል፡፡
ብሔሮች ያላቸውን መልካም እሴቶች በጥሩ ጐኑ መጠቀም ተገቢ ቢሆንም ለአገሪቱና ህዝቧ ጠንካራ አንድነት ግን እንቅፋት እስኪሆን አይደለም፡፡
የአመለካከት ልዩነት ተፈጥሯዊ መብት ሆኖ ሳለ ልዩነቱ የአገሪቱን ሕግ እስካልጣሰ ድረስ የልዩነት አመለካከቶች እንዳይገለፁ ቀድሞ መንቀሳቀስ ቢያንስ በአሉታዊ ጐኑ ያስገምታል፡፡ የህጉና አተገባበሩ ልዩነት በተለያዩ ቢሮክራሲዎች የተጠለፈና ሌሎች |አላማዎችን´ የማስፋፋት ድባብ ያለው መምሰል የለበትም፡፡ የመንግስትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተልዕኮ መሬት ላይ ካሉት እንቅስቃሴዎች፣ ውስጥ ለውስጥ ከሚፈፀሙብን አስገራሚ ጥፋቶች አንፃር ነው መመዘን ያለበት? ወይንስ ዕውነታውን እየሸሹ በየጊዜው ሊነገር ከሚሞከረው ድብልቅልቅ ምስል? እየተፈፀመ ያለው ጥፋት ነው፤ በቂ ማስረጃም  አለ፤ ከተባለና ይህንንም እያወቁ ያላወቁ መምሰል ልክ ግዴታን መብት፣ መብትን ደግሞ ግዴታ አድርጐ ለመንቀሳቀስ ስለተሞከረ የአምባገነንነትን ዝንባሌ ከማሳየቱ ሌላ ምን ፋይይ አለው? በዚህ ሁሉም ስህተት ይስተካከላል? አንዳንድ ሀሣቦች ሊገለፁ ሲሞክሩ ውስጥ ለውስጥ ለማደናቀፍ ሲሞከርስ? እያንዳንዱን አስገራሚ ክፍተት እዚህ መዘርዘር ስለማያመች ነው፡፡
እየሆኑ ያሉ በርካታ ጥፋቶች ሥርዓቱ በረiም ዘመናት ውስጥ |ማምረት´ የሚገባውን አማራጭ የሲቪል መሪዎች መጠን ቸል በማለቱ ጭምር የገባበት ማጥ መሆኑ አሌ ሊባል አይችልም፡፡
አሁን ሊወሰዱ ከሚገባቸው እርምጃዎች መካከል ግን አንዱ ሙያዊ ነፃነትን ለማስከበር አቅሙ ያላቸው ይህን መፈፀም፣ እያደጉ የመጡ ለየት ያሉ ወንጀሎችን ማዳከም፣ እነዚህን ኃላፊነቶች ለመወጣት ፍላጐት የሌላቸውን ያለ ቅድመ ሁኔታ ዞር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

 

Read 3436 times Last modified on Saturday, 08 October 2011 09:24