Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 October 2011 12:55

..መዝናናት መዝናናት፣ አሁንም መዝናናት!..

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጓድ ሌ ጓድ ሌኒን ኒን
George Gordon, Lord Byron
“If I should meet thee after long years,
How would I greet thee? In silence and tears” Lord Byron
የተከበራችሁ አንባብያን
ባለ ቅኔው George Gordon እንደ ፀሐፊ Romanticism የሚባለውን የስነጽሑፍ ዘርፍ የሚወክል፣ ሲሆን እንደ ግለሰብ ደግሞ በውርስ የመሳፍንት ዘር ስለሆኑ Lord Byron ይባላሉ፡፡

ሰውየው ድንቅ ባለቅኔ በመሆኑ፣ እና ጠባዩ አስቸጋሪ ስለነበረ፣ እና በውበቱ የኤውሮፓን መሳፍንትና መኳንንት ሴቶች ያማለለ ሴት አዋይ ስለነበረ፣ እና ከዚህ በላይ ደግሞ ሞት የማይፈራ የጦር ሜዳ ጀግና ስለነበረ በዚህ ሁሉ ምክንያት በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን የኤውሮፓ ታሪክ ውስጥ እጅግ የጐላ የዘመኑ ቁንጮ ሆኖ ይታያል፡፡
የመልኩ ማማር ..ከአማልክቱ እንደ አንዱ የዋበ.. እስኪባልለት ድረስ ቢሆንም፣ አንድ እግሩ ቆልማማ ነበረ፡፡ ይህም inferiority complex (የበታችነት ስሜት) አሳደረበት፡፡ በዚህ የተነሳ ነበር ጠባዩ ለሴቶች እጅግ አስቸጋሪ የሆነው፡፡
የአክስቱ ልጅ ሲበዛ ቆንጆ ስለነበረች፣ ቆንጆ ለቆንጆ ተፋቀሩ፡፡
በነሱ ባህል ይህ ዝምድና ጋብቻን አይከለክልምና ስለተዋደዱ በህግ ተጋቡ፡፡ በነጋታው ጧት ወደ ጫጉላ ሽርሽር (Honey moon)  ይሄዳሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ እሱ ሙሽሪቱን   ማለዳ ተነስቶ ጥሎ ኮበለለ፡፡ በኤውሮፓ ታላላቅ ከተማዎች እየተዘዋወረ ሴቶችን እያማረጠ ሲደሰት (እና ቅኔዎችን ሲያፈልቅ) አመታት አሳለፈ፡፡
...ይሄ ሁሉ ሲሆን ሳለ፣ እዚያ ማዶ ግሪክ አገር ለዘመናት የቱርክ ቅኝ ግዛት ሆና ቆይታ፣ ለነፃነትዋ መዋጋት ከጀመረች አመታት ተቆጥረዋል፡፡
እስከ ዛሬ ሴቶች እያማረጡ መደሰት ባይረንን ሳይሰለቸው ይቀራል? ለማንኛውም ወደ ለንደን ተመለሰና፣ በትልልቆቹ ጋዜጣዎች ለእንግሊዞቹ የሚከተለውን መልእክት እየደጋገመ xs‰=§cW:-
Rule Britanina, Britania rule the waves;
Englishmen never shall be slaves
እያልን ስንዘምር አለማፈራችን ሊያሳስበን ይገባል፡፡ ምክንያቱም እኛ የነፃነትን ዋጋ የተማርነው ከጥንት ግሪካውያን ነው፡፡ ስነ ጽሑፍንም፣ ቅርፃ ቅርጽንም፣ ስእልንም፣ አርኪቴክቸርንም፣ ፍልስፍናንም እሴታችን ያደረግናቸው ከጥንት Athens ተምረን ወርሰን መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ከዚህም ጋር ግሪካውያን ለነፃነታቸው እየተዋጉ መሆናቸውን በየእለቱ ጋዜጣዎቻችን ውስጥ እናነባለን፡፡
Great Britain ዛሬ የባህር ንግስት ናት፡፡ ለግሪኮቹ ልትደርስላቸው በተገባ ነበር፡፡ ብቻ የመንግስትን ጉዳይ ለመንግስት እንተወውና፣ በግለሰብነታችን ገንዘብ እናዋጣ፣ እኔ ለቁስለኞች መድሀኒት፣ ፋሻ፣ ብርድ ልብስ ጭኜ ለመነሳት ሶስት መርከብ አዘጋጅቼ፣ የናንተን እርዳታ በመተማመን እየጠበቅኩ እገኛለሁ፡፡
አላማው ተሳካለት፡፡ ጭኖ የሄደውን ሁሉ አስረክቦ ሲያበቃ፣ ለትጥቅ ትግል ወደ ጦር ሜዳ ዘመተ፡፡
በአመቱ ወደ ለንደን ተመልሶ፣ እንደ በፊቱ ለቁስለኞች አስፈላጊ የሆነ መድሀኒትና እህል ብቻ ሳይሆን የጦር መሳሪያም ጭምር በሶስቱ መርከብ ጭኖ ወደ አቴንስ ተመለሰ፡፡ አስረክቦ ዛሬም ወደ ጦር ሜዳ መረሸ፡፡
ዳሩ ምን ይሆናል? እሱ እንደተመኘው ወይ ግሪክ ነፃነቷን ስትቀዳጅ አላየ፣ ወይ በጦር ሜዳ አልሞተላት፡፡
ያን የመሰለ ጀግና የሮማንቲሲዝም ተምሳሌት፣ በተፋፋመ ጦርነት መሀል እየተታኮሰ መስዋእት መሆን ሲገባው በተራ አልባሌ በሽታ ሞተ (የበሽታውን ስም እንኳ ረስቼዋለሁ፣ influenza ይመስለኛል እንጂ)
George Gordon, Lord Byron መካነ መቃብር አቴንስ ውስጥ የክብር ቦታ አለው፡፡ ማንም ቱሪስት guided tour ሲወስድ (ማለት ዋነኛ ስፍራዎችን ሲ ገ በ Ÿ) Parthenon የሚባለውን የቤተ መቅደስ አምባ (One of the seven wonders of the world ytÆlWN) ካደነቀ በኋላ፣ y Lord  Byron N መካነ መቃብር ያስጐበኙታል፡፡
ባይረን ከድቷት ከኮበለለ በኋላ፣ ለፍቅረኛው የፃፈላት ግጥም እነሆ ለማሳረግያ
To His Mistress
When we two parted in silence and tears,
Half broken hearted to sever for years;
Pale grew thy cheek and paler thy brow
I felt a foreboding of what I feel now
If I should meet thee after long years
How should I greet thee? In silence and tears!
ሶስት አይነት ይሁዳ
Borghes (ቦርሄስ) የሚባለው አይነ ስውር አርጀንቲናዊ ደራሲ የኖቤል ሽልማትን ተቀብሏል፡፡ ግጥሞችና አጫጭር ልቦለዶቹን በእስፓኝ ቋንቋ ይጽፋቸዋል፡፡ አባቱ እንግሊዝ ስለሆነ፣ እንግሊዝኛን ከአፍ መፍቻ ቋንቋው እኩል ይችለዋል፡፡
ስለዚህ ጽሑፎቹን ሁሉ እሱ ራሱ ነው ወደ እንግሊዝኛ የሚተረጉማቸው፡፡
መጣጥፍ ይሁኑ ወይስ ልቦለድ ያልለየላቸው ጽሑፎችም አሉት፡፡ ከነዚህ አንዱ Three versions of Judas ይባላል፡፡
ይሁዳ አንድ ሀሙስ ማታ ጌታ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እራት ሲበላ፣ ለይሁዳ አጐረሰውና ..የምታደርገውን ፈጥነህ አድርግ.. አለው፡፡ ይሁዳም ወጣ፡፡
በጌቴሲማኒ በሌሊት ..ይሁዳ መጣ፣ ከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከፃፎች፣ ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ፡፡  አሳልፎ የሚሰጠውም ..የምስመው እርሱ ነው፣ ያዙት.. ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር፡፡
መጥቶም ወድያው ወደ እርሱ ቀረበና ..መምህር ሆይ.. ብሎ ሳመው፤ እነርሱም እጃቸውን በእርሱ ላይ ጭነው ያዙት፡፡
ኢየሱስም ..ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን? በመቅደስ እለት እለት እያስተማርኩ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝም፤ ነገር ግን መፃሕፍት ይፈፀሙ ዘንድ ይህ ሆነ.. አላቸው፡፡
በዚህ እንደምናነበው (ይለናል Borghes) ይሄ ቀሽም ይሁዳ በልቦለድ ቢነበብ እንኳ ኢተአማኒ ነው፡፡ የማይመስል ነገር!
ይሁዳ ሁለት ኢየሱስ በሱ ጠቋሚነት ተይዞ፣ ተፈርዶበት፣ ተገርፎ፣ መስቀሉን ተሸክሞ ጌቴሴማኒ ድረስ ተወስዶ ተሰቀለ፡፡
ይሁዳ በሰራው ሀጢአት ተፀቶ፣ ምህረት እንደማይገባው ተገንዝቦ፣ መምህሩን በሸጠበት ሰላሳ ብር መቃብር ገዛ፡፡
..አኬል ዳማ.. (የመቃብር ዋጋ) ብሎ ሰየመው፡፡ እና ራሱ ታንቆ ሞተ፡፡ ይሄኛው ይሁዳ ደግሞ ልቦለድ ቢሆን ኖሮ ..ቀሽም የጀማሪ ሙከራ.. ተብሎ ይታለፍ ነበር፡፡
ይሁዳ ሶስት Borghes የሚመርጠው ይኸኛውን ነው፡፡ እንደዚህ ይለናል፡፡ አስራ አንዱ ደቀ መዛሙርት አሳ አማጅ፣ ገበሬ፣ እና ሌላ ተራ ሰው አይነት ነበሩ፡፡
ይሁዳ ግን ምሁር ነው፣ ኧረ የማህበሩ ገንዘብ ያዥ እሱ ነው እና ሲያስብ ሲመራመር ምን ያስተውላል? የኢየሱስ ስቅላት ለአዳምና ሄዋን ልጆች የመጨረሻው ታላቅ ትራጀዲ ነው፣ መአት ነው፡፡
እዚህ tragedy ውስጥ ዋናው ጀግና (hero) ኢየሱስ ሲሆን፣ የሚፃረረው ከይሲ ጀግና (Villain) ግን የለም!
ጐደሎ አንካሳ ትራጀዲ ነው፡፡ ይሁዳ ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ብቻ ሳይሆን፣ መልእክቱ በትክክል የገባው ሰው እሱ ብቻ ነበር (ለሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ይህ ሀቅ የተገለፀላቸው ኢየሱስ ከሙታን ተነስቶ ካረገ በኋላ መንፈስ ቅዱስን (..ጴንጤቆስጥን..) ሲልክላቸው ጊዜ ብቻ ነበር) እና ጀግናው ይሁዳ እቅድ አወጣ፡፡ ለአንድየው ኢየሱስ ተመመጣኝ ከይሲ ተፃራሪ ገፀባህሪ (Villain) ሆነ፡፡ ሸጠው፣ በጨለማ አስያዘው፣ ወደ ስቅላቱ ላከው፡፡
ነገር ግን፣ ጌታውን ስለሸጠ  ከልብ ተፀፀተ፡፡ ከልቡ አልቅሶ ሀጢአቱን ቢናዘዝ ጌታ ኢየሱስ ይቅር እንደሚለው እርግጠኛ ነው፡፡ እንዲህ ካደረገ ግን ከሀዲነቱ ቀሽም ኢተአማኒ ልቦለድ ይመስልበታል፡፡
የሚያስፈልገውኮ ታድያ የምር ሀቀኛ (Villain) ነው፡፡ ስለዚህ፣ ራሱን ካጠፋ ገሃነብ እሳት እንደሚጠብቀው ያውቃል፡፡
እና ኢየሱስ የሚመጥነውን ከይሲ ገፀባህሪ አገኘ፡፡ ደቀ መዝሙሩ ይሁዳ ለሱ ሲል ለዘለአለም ስለተኰነነለት የኢየሱስ ትራጀዲ ሙሉ እና artistic ሆነ!
ያነበብነውን በልባችን ያሳድርልን፤ አሜን!!
ሼክ አብዱራህማን
ይቅርታ አድርጉልኝ፣ ቅድም ስጣደፍ ረስቼ ያልነገርኩዋችሁ አለ፡፡ ይኸውም ቦርሄስ አረብኛን ከእስፓኝኛና ከእንግሊዝኛ እኩል ይናገራል ይጽፋል፡፡ የአረብ ስልጣኔን እጅግ በጣም የሚያደንቅ ..ቲፎዞ.. ነው፡፡ ..ሼክ አብዱራህማን.. የምትባል አጭር ልቦለዱ እንዲህ እንዲህ TtrµlC:-
ሼክ አብዱራህማን ገና ከልጅነታቸው አንስቶ የአላህ ፍቅር አደረባቸው፡፡ እያደጉ ሲሄዱም ፍቅራቸው እየሰፋ እየጠለቀ ..መንፈሳዊ እብደት.. ሆነ፡፡ ማለትም በብዛት ይጓዙ ነበረ፣ በየሄዱበትም ያንን መስጊድ ያሳንፃሉ፣ ይህን መድረሳ (መንፈሳዊ ትምህርት ቤት) ይከፍታሉ፣ ያንን ያቅዳሉ፡፡ ሀሳባቸውን፣ እቅዳቸውን፣ ስራቸውን ሁሉ አላህ ሞላው...
...አንድ ቀን ረፋድ ላይ ይህንእያሰላሰሉ፣ የት እንደደረሱ እንኳ ሳይታወቃቸው ድንገት ብንን ብለው ቢነቁ የጦፈ ውጊያ መሀል ላይ ናቸው፣ ወታደሮቹ በጨበጣ እየተፋጁ ነው፡፡
ከወድያ የተወረወረ ጦር ደረታቸው ላይ ሊተከል ሲል በደመ ነፍስ የአላህን ስም ጠሩ (አእምሮዋቸው ውስጥ  ያ ሁሉ ሊከፍቱት የነበረ መድረሳ፣ ሊያሳንፁት የነበረ መስጊድ፣ ሊያቋቁሙት የነበረ ማህበር ውል አላቸው)
ጦሩ ደረታቸውን ሊበሳቸው አንድ ክንድ ያህል ሲቀረው በአየር ላይ ቀጥ ብሎ ረግቶ ቀረ - እንደተንጠለጠለ ...ሼኩ አልፈውት ሄዱ፣ ከውጊያው ራቁ፡፡ ያን ሁለ እቅድ ለመፈፀም ረዥም አመታት ወሰደባቸው፡፡ ተግባራቸውን እንደፈፀሙ ሲያስተውሉ ጊዜ፣ በጥልቅ እፎይታ ..ተመስገን አላህ.. አሉ፡፡
እና በዚያች ቅጽበት ወደዚያ ወደ ተፋፋመው ውጊያ መሀል ተመልሰው ቀና ቢሉ
ያ ሊበሳቸው አንድ ክንድ ያህል ሲቀረው በቅጽበት ቀጥ ብሎ ረግቶ ቀርቶ የነበረው ጦር ጉዞውን ቀጠለ - ደረታቸው ውስጥ ተሰካ...
አላህ ለሚያፈቅሩት ተአምር ይሰራል፣ ግን የፈጠረውን ህግ ቅጽበት ታህል እንኳ አያፋልስም!
ቸር ይግጠመን ኢንሻላህ!

የቦርሄስ ህይወት - በአጭሩ
Buenos Aires  ተወልዶ ያደገው ቦርሄስ በሃያ አመታት እድሜው በአርጀንቲና በጣም የተወደደ ገጣሚ ነበር፡፡ እናቱና ጓደኞቹ የስነ ጽሑፍ እንቁ ነው ብለው ቲፎዞዎች ሆነዋል፡፡ የፃፈውን ረቂቅ በታይፕ ሊገለብጡለት ሁልጊዜ ዝግጁ ነበሩ፡፡ ኧረ ቢላላኩለት ደስታቸው ነው፡፡
Lewis Jorge Borghes እድሜው ወደ ሰላሳ በተጠጋ መጠን አይኑ እየደከመ ሄዶ፣ በመጨረሻው ታወረ፡፡
አይኑ እየከዳው መሄዱ አጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞችን የመፃፍ ሂደቱን በምንም አልቀነሰውም፡፡
ቦርሄስ አርባ አመት ካለፈው በኋላ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቤተ መፃሕፍት
አስተዳዳሪ ለመሆን የሚፈልጉ ሰዎች መረጃቸውን ይዘው መጥተው እንዲያመለክቱ የሚል ማስታወቂያ ተሰራጨ፡፡ እናቱና ጓደኞቹ ለቦታው ስለምትመጥንና እንሂድ አመልክት አሉት፡፡ ሰው ጠፍቶ ነው ወይ እውር የሚቀጥሩት ቢላቸው ..አንቀበልም ይሉሃል እንጂ ሌላ ምን እንዳይመጣብህ ነው? ይልቅስ ተነስ እንሂድ.. ብለው ጓደኞቹ አጅበውት ሄደ፡፡
ባለስልጣናቱ interview ሲያደርጉት ዘጠኝ ቋንቋ የሚያውቅ መሆኑን እና ሌላ ሌላም ከነገራቸው በኋላ ..ለዚህ ስራ ብቃት አለኝ የምትልበትን ንገረን.. ሲሉት
..ስለ ማስታወቅያችሁ እንደ ሰማሁ አሰብኩበት፡፡ ለካስ እኔ ሳይታወቀኝ፣ ለዚህ ስራ ሃያ አመት ሙሉ ተዘጋጅቼበታለሁ.. ብሎ መለሰ፡፡
እዚያው በዚያሙ ተቀጠረ፡፡
እንዴት እንደሚጽፍ ቦርሄስ ራሱ nGéÂL:-
እንደ አይናማ ዘመኑ ቢሮው ቀጭ ብሎ በምናብ ወረቀቱን ያወጣና የመጣለትን ሃሳብ በምናብ ይጽፋል፣ ይሰርዛል ይደልዛል፣ እመጫት አረፍተ ነገር ይጨምራል፣ የግርጌ ማስታወሻ ያክልበታል፣ ወዘተ፡፡ አራት ገጽ ፃፈ እንበል፡፡
በነጋታው ቢሮው ቁጭ ብሎ በምናብ የትላንቱን አራት ገጽ ያነባል፣ ትላንት የተደረገው መሰረዝ፣ እመጫት መጨመር፣ የግርጌ ማስታወሻ ይሄ ሁለ ወለል ብሎ እየታየው፣ እዚሁ ላይም ሌላ  ለውጥ ያደርጋል እንዳስፈላጊነቱ፡፡
እንዲህ እያደረገ ጽሑፉ ሲያልቅ ለናቱና ለጓደኞቹ ያነብላቸዋል፡፡ እነሱ በታይፕራይተር ይመቱለታል፡፡
ወይ ውድቀታቸውን ወይ ሞታቸውን የሚጋብዙ
አንድ
በጃንሆይ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት በመጨረሻዋ አመት አንድ የመጠጥ ግሮሰሪ ውስጥ ሳላውቀው አንድ ዘንካታ አዛውንት አጠገብ ተቀመጥኩ፡፡ ቀስ እያልኩ ከሁኔታቸው እንዳስተዋልኩ ሞቅ ብሏቸዋል እንጂ አልሰከሩም፡፡
ባንዳንድ ሁኔታ ውስጥ አጠገባችን የተቀመጠው ጠጪ አይተነው የማናውቅ ከሆነና ከዛሬ በኋላ እንደማናገኘው እርግጠኛነት ከተሰማን፣ ለነብስ አባታችን እንኳ የማንናገረውን ስሜትና ሀሳባችንን እንዘከዝካለን፡፡ እኚህም ሰውዬ ይናዘዙልኝ ጀመር፡፡
..እኔ በጣም ሀብታም ነኝ ልንገርህ፣ ጐበዝ.. አሉኝ ..ከቅማያታችን በፊት ጀምሮ የሀብታም ዘር ነኝ፡፡ ከፋ አርባ ጋሻ የቡና መሬት አለኝ፡፡ ጤፉ ከአድአ ይጫናል፣ ማሩ ከጐጃም፣ ቅቤው ከሸኖ፡፡ ኧረ ስንቱን ልንገርህ
..ድህነት እንኳን እኔ ጋ ልትደርስ ይቅርና፣ የልጅ ልጆቼ ቤት እንኳ ደፍራ አታንኳኳም..
ከጨረሱልኝ በኋላ አብረውኝ መቆየት ለሁለታችንም የሚከብድ መሆኑን አይተው ይመስለኛል ..በል ደህና እደር፣ ጐበዝ.. ብለው ጨብጠውን ወጡ፡፡
እጅግ በጣም ያስገረመኝ፣ ለባህል ልማድ ወይም ለይሉኝታ ያህል አንዲት ጊዜ እንኳ ..ፈጣሪ ይክበር ይመስገን.. ወይም ..እመብርሃን ትወደኛለች መቸስ.. ወይም እንዲህ የመሰለ ቃላት አልተናገሩም...
...ከአንድ አመት በኋላ ጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ሃይለማርያም የአድሀርያን ትርፍ ሀብት ሁሉ መወረሱን በአዋጅ አስታወቁ፡፡
ሰፊው ህዝብም እሁድአብዮት አደባባይ እየወጣ፣ ደረቱን እየመታ ሙሾ
እንግዲህ ቀረ ሳይሰሩ መብላት፣ ሳይሰሩ መብላት!..  
ሁለት
እከተማው ዳር፣ አንድ አነስተኛ ወንዝ አጠገብ አንድ ሰፊ ግሮሰሪ አለ፣ ጢቅ ብሎ ሞልቷል፡፡ እኩለ ሌሊት ሊደርስ ስለሆነ ሰው መውጣት ጀምሯል፡፡
አንድ የሰከረ ሰውዬ እየተንጐራደደ ሸለለ
..ኑሮ ነው ወይ፣ ኑሮ ነው ወይ የሸማኔ ኑሮ?
ከወገቡ በታች እመሬት ተቀብሮ?..
ሌላ ሰውዬ ተነሳና፣ ሳይሸልል
..ሸማኔማ ባይኖር፣ ሸማኔማ ባይኖር
ይህ ጋንዲላ ቂጥህ ማን ያለብሰው ነበር?.. ብሎ ካነበነበ በኋላ፣ ከኪሱ ሽጉጥ አውጥቶ በሸላዩ ደረት ላይ ሁለት ጥይት ቆጠረበት፡፡ ፈጥኖ ሲወጣ ጠጪዎቹ በምክርና በመረጃ ሸኙት፡፡
..ባቡር መንገዱ ስትደርስ ወደ ቀኝ ታጠፍ፣ ሄደህ ድልድይ ታገኛለህ አትሩጥ ዘና ብለህ ተራመድ ሽጉጥህን ወንዙ ውስጥ ጣለው..
ሶስት
አራዳ ውስጥ፣ ከማዘጋጃ ቤቱ ፊት ለፊት መንገዱን ተሻግሮ፣ አንድ ሰውዬ  Volkswagen መኪናው ውስጥ ተቀምጦ የቀጠረው ሰው እስኪመጣ ይጠብቃል፡፡ አለድ ቆማጣ መጥቶ፣ በተከፈተው መስኮት ..ስለአቡነ አረጋዊ ስለ ገብረክርስቶስ.. ሲል ለመነው፡፡
..እግዜር ይስጥህ.. ቢለው
..እግዜርማ ቢሰጠኝ አንተን ምን አስለመነኝ?.. ብሎ በድንገት እጁን አስገብቶ በጣቶቹ ጐማዳ የሰውየውን ፊትና አፍ በቁጭት እሽትሽት አደረገው
ሰውየው ሽጉጥ መመዘዘና በግምባሩ ለቀቀበት፡፡
(እጥር ምጥን ያለች አስቀያሚ ታሪክ ቢሆንም፣ እንዳይሰለቸን ለለውጥ ያህል ስለሆነ ምንም አትል)   
አራት
አንድ ቀን ሀረር ውስጥ፣ ሰባት ሆነን በርጫ ላይ ቆይተን፣ የምርቃን ድባብ ውስጥ ነን፡፡ ሰው በፈጣሪ ስራ ውስጥ ጥልቅ ካለ፣ መዘዝ ማስከተሉ አይቀርም እያልን ስንፈላሰፍ ቆይተናል፡፡ (የሚከተሉት የእውነት ታሪኮች ውስጥ ሚና የሚጫወቱትን ገፀባህሪዮች እነዚህ ስድስቱ ያውቁዋቸዋል፣ የሰፈር ልጆች ናቸው አንዳንዶቹ፡፡)
ለዚች ላሁንዋ ትረካችን ስም አያሻቸውም፡፡
ሰውየው ገንዘብ ከፍሎ ላሙን ለማስጠቃት ምርጥ ወደተባለ ኰርማ ወሰዳት፡፡
ላምና ኰርማ እስኪቀራርቡ እስኪሸታተቱ ድረስ፣ ባለኮርማ
..ለአገልግሎታችን ዋጋ አንድ ብር ጨምረናል.. ይላል፡፡
..አይደለም አንድ ብር፣ ቀይ ሳንቲም አልጨምርም..
ባለ ኮርማ ..እንግድያው ላምህን ይዘህ ወደምትሄድበት ሂድ.. ብሎ ኮርማውን ከላምዋ ለመለየት በትከሻው ሊስበው ሲል፣ በሬው በቀንዱ ወደ ጐን ቃጥቶ ሆዱ ውስጥ ሰካበትና፣ ለስሪያ ዘለለ፡፡ ሰውየው ቀንዱ ላይ ሞተ፡፡
•YHN በምናወራበት ቀን ድራማው የተከሰተበትን ቦታ ጋይዶች ታሪኩን እየተናገሩ ለሀገር በቀል ቱሪስቶች ያስጐበኙ ነበር፡፡
በሰፈሩ በመልክ የታወቀና የተመሰገነ ..ኮርማ.. ድመት አለ፡፡ አንዲት ሴትዮ በጣም የምትወዳትን ድመት ከፍላ ልታስጠቃ መጣች፡፡ ልክ ድመቶቹ ጩኸታቸውን ጨርሰው ስሪያው ሊጀምር ሲል የድመቶች ባለቤቶች ድሮ ተኝቶ የነበረው ቁርሾ ተቀሰቀሰባቸው፡፡ ..ያንተን ክፋት ማስታወሻ እንዲሆነኝ ብዬ ነው ለዚያውም ካንተ እምገዛው? የመንደር ቂል መስዬሃለሁ እንዴ? ሆ.. እያለች ድመትዋን በወገብዋ አንስታ ስትስብ፣ ኮርማው አይኗን ቧጭሮ አፈሰሰላት፡፡
ይህንና የመሳሰለውን እሰው ላይ የሚደርሰውን ትራጀዲ እያወራን በሳቅ መንከትከታችንን ባስታወስኩት ቁጥር ያስገርመኛል፡፡ ምክንያቱን የሚያውቅ ሰው ይኖር ይሆን? ኖረስ አልኖረ ልዩነት ያመጣ ይሆን?
ለማንኛውም ቸር ይግጠመን፤ አሜን!

 

Read 4274 times Last modified on Saturday, 01 October 2011 12:59