በውድድሩ ላይ የሰአት መቆጣጣርያ ቺፕ በተገጠመላቸው ጫማዎች ሁሉም አትሌቶች በመወዳደራቸው ተሳታፊዎች ርቀቱን የሚጨርሱበትን ጊዜ ለማወቅ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል ያሉት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች የተሳታፊዎች ደረጃና የገቡበት ሰአት ውድደሩ ከተገባደደ በኋላ በሁለት ሰአት ግዜ ውስጥ በድረገፃቸው ይፋ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኮካኮላ የ7 ኪሎሜ ተከታታይ ሩጫ ውድድርን ያዘጋጀው ጤናማ አኗኗርን ለማስፋፋት ባነገበው መርህ ነው፡፡ ቀጣይ ውድድሮች ከ3 ሳምንትና ከ2 ወራት በኋላ እንደሚቀጥሉም ታውቋል፡፡ በውድድሩ በአጠቃላይ 200ሺ ብር ለሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን በ3ቱ የኮካኮላ ሲሬዬስ ውድደሮች በመሳተፍ በሁለቱም ፆታዎች ለሚያሸንፉ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 50ሺ ብር እንደሚበረከት ታውቋል፡፡