በዝግጅቱ ከጉራጊኛ ታዋቂ ድምፃውያን እነ ፀጋዬ ሥሜ እና መውደድ ክብሩ ያቀነቅናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ..የሳምንቱን መስቀል በዓል በአንድ ቀን.. የሚል ዝግጅት በዮድ አቢሲኒያ፣ ባህላዊ ምግብ ቤትና በጉራጌ ባህል ማእከል ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ነገ ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ዮድ አቢሲኒያ ምግብ ቤት በአውደርእይ ታጅቦ ይካሄዳል፡፡ በዚህ ዝግጅት ድምፃውያን ሃይሉ ፈረጃ፣ መውደድ ክብሩ፣ ምናሉሽ ረታ፣ ሚሊየን ማሃመድና ሌሎች ተገኝተው ያቀነቅናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሪት ሊዲያ ፍቅሬ ገልፃልናለች፡፡
በሌላም በኩል የደንጌሳት ምሽት ሐሙስ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት በቬልቬት የምግብ አዳራሽ ፣ ማክዳ የባህል አዳራሽ ቀረበ፡፡ የጉራጌን ሕዝብ ታሪክና ባህል ጠብቆ በቀረበው ዝግጅት ታዋቂ ድምፃውያን ሥራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን የባህል ዝግጅቱ በምግብና መጠጥ ፌስቲቫልና በችቦ ማብራት ታጅቧል፡፡ በዝግጅቱ ካቀነቀኑ ድምፃውያን መካከል ፀጋዬ ስሜ፣ ምናሉሽ ረታ፣ እና ፈቀለ ማሩ ይገኙበታል፡፡