Saturday, 20 April 2019 13:43

የአፄ ኃይለሥላሴ የመስቀል ስጦታ ከፈረንሳዩ ካቴድራል ቃጠሎ ተረፈ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

 ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እ.ኤ.አ በ1954 ፈረንሳይን በጐበኙበት ወቅት ለኖተርዳም ካቴድራል በስጦታ ያበረከቱት የኢትዮጵያ ጥንታዊ የመስቀል ስጦታ በሠሞኑ የካቴድራሉ ቃጠሎ ጉዳት ሳይደርስበት ከእሳት መትረፉ ተገለፀ፡፡
ጃንሆይ ከ65 አመት በፊት ፈረንሳይን በጐበኙበት ወቅት ለካቴድራሉ በስጦታ ያበረከቱት መስቀል ምንም አይነት ቃጠሎ ሳይደርስበት መትረፉን በቲውተር ገፃቸው ያስታወቁት በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ምክትል ልኡክ መሪ ኢማኑኤል ፔስኔር መስቀሉም ከሌሎች ከእሳት የተረፉ ጥንታዊ ውድ ቅርሶች ጋር ወደ ሌ ሉቨር ሙዚየም መዘዋወሩን ገልፀዋል፡፡ ካቴድራሉ በተቃጠለበት ወቅት ከ850 አመታት በላይ እድሜ ያላቸው ውድ ቅርሶችና ሃይማኖታዊ መገለጫዎች መውደማቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል የፈረንሳይ ነገስታት ዘውዶችና ጥንታዊ ስዕሎች ይገኙበታል ተብሏል:: የ850 አመታት እድሜ ያለውና በአመት ከ14 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች የሚጎበኙትን ይህን ታላቅ ካቴድራል በፍጥነት መልሶ መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታውቀዋል፡፡

Read 8025 times