አድርገውት ከሆነ በእድሜ ልክ እስራት ሊቀጡ ይችላሉ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ፣ ከሟቹ የሊቢያው አቻቸው ሙአመር ጋዳፊ 30 ሚሊዮን ዶላር ተቀብለዋል በሚል ከሰሞኑ የወጣውን ዘገባ ፍጹም ውሸት ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ማስተባበላቸው ተዘግቧል፡፡
ሰንደይ ታይምስ ሰሞኑን ባወጣው ዘገባው፤ ጃኮብ ዙማ ከጋዳፊ ብዙ ገንዘብ ተቀብለዋል፤ በህገወጥ መንገድ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ከሊቢያ ወደ ደቡብ አፍሪካ አሸሽተዋል ማለቱን ተከትሎ፣ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ መሰንበቱን የገለጸው ቢዝነስ ኢንሳይደር፣ በእርግጥም አድርገውት ከሆነ በእድሜ ልክ እስራት ሊቀጡ እንደሚችሉ መነገሩን ጠቁሟል፡፡
ጃኩብ ዙማ ከስምንት አመታት በፊት የሞቱትን ጋዳፊን በህይወት እያሉ ለመጨረሻ ጊዜ በአካል ያገኙ መሪ እንደነበሩ ያስታወሰው ዘገባው፤ በወቅቱም ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከሊቢያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማሸሽ ሳያሴሩና ተግባራዊ ሳያደርጉት እንዳልቀሩ መነገሩን አመልክቷል፡፡
የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ባለሙያዎች ጃኩብ ዙማ ከጋዳፊ 30 ሚሊዮን ዶላር መቀበላቸውን የሚያመለክት መረጃ እንዳገኙ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት ራሞፋሳ ጥቆማ መስጠታቸውንና በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ ሳይጀመር እንዳልቀረም ሰንደይ ታይምስ ባወጣው ዘገባ ገልጧል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል