Wednesday, 27 February 2019 13:04

ጀርመን በየአመቱ ከ260 ሺህ በላይ ስደተኞች ያስፈልጓታል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

    አውሮፓዊቷ አገር ጀርመን የሰው ሃይል ፍላጎቷን በአግባቡ ለማሟላት በመጪዎቹ አራት አስርት አመታት ጊዜ ውስጥ በየአመቱ ቢያንስ 260 ሺህ ያህል ስደተኞች እንደሚያስፈልጋጓት አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡
ጀርመን አብዛኛው የህዝቧ በእርጅና ዘመን ምዕራፍ ላይ የሚገኝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተፈጠረባት የሰራተኛ የሰው ሃይል እጥረት እየተባባሰ እንደሚገኝ የዘገበው ዘ ኢንዲፔንደንት፤ ይህንን ክፍተት ለመሙላት በየአመቱ ከ260 ሺህ በላይ የሌሎች አገራት ስደተኞችን አስገብታ ወደ ስራ ማሰማራት እንደሚገባት በጥናቱ መገለጹን አስታውቋል፡፡
ጀርመን የሰው ሃይል ፍላጎቷን ለማሟላት በየአመቱ ማስገባት ከሚጠበቅባት ስደተኞች መካከል 146 ሺህ ያህሉ የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆኑ አገራት ዜጎች መሆን እንዳለባቸውም ብሬልስማን ፋውንዴሽን የተባለው ተቋም ያወጣው ጥናት አመልክቷል፡፡ የጀርመን የህዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ እስከ 2016 ድረስ ከ30 በመቶ በላይ ይቀንሳል ተብሎ እንደሚገመት የጠቆመው ጥናቱ፣ ይህም የአገሪቱን ኢኮኖሚ አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ አገሪቱ ስደተኞችን በማስገባት የሰው ሃይል እጥረቷን ማቃለል እንደሚገባትና ለዚህም ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር የስደተኞች ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደሚኖርባት መክሯል፡፡

Read 1312 times